info@eastgojjam.gov.et   058771 1950 /0587713994 ENአማ
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ግባ

ዜና አጠቃላይ · Nov 28, 2026

የሴቶችን ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል በቅንጅትና በትብብር መስራት ይገባል።

የሴቶችን ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል በቅንጅትና በትብብር መስራት ይገባል።
***
ህዳር 16/2019 ዓ.ም(ምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ) በምስራቅ ጎጃም ዞን በዓለም ለ35ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ለ21 ኛ ጊዜ ለሚከበረው የፀረ- ጾታዊ ጥቃት የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
የንቅናቄ መድረኩ "ለተጎጅዎች ፍትህ፣ ለወንጀለኞች ተጠያቂነት፣ ለሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ደህንነት!" በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል።
በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የምስራቅ ጎጃም ዞን ሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ተወካይ ኃላፊ አቶ ተማረ አበባየ እንደገለጹት የሴቶችን ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል በቅንጅት እና በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል።
መድረኩ ለተጎጅዎች ፍትህ የምንሻበት፣ ወንጀል የሚፈጽሙትን ተጠያቂ የሚደረጉበት እንዲሁም የታዳጊ ሴቶችን ደህንነት እንዲጠበቅ ምክክር የሚደረግበት በመሆኑ ችግሩን እንዴት ማስቆም እንደሚገባ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ የጋራ አቋም የሚወሰድበት መድረክ መሆኑን ተወካይ መምሪያ ሀላፊው አመላክተዋል።
የንቅናቄ መድረኩ እስከ ህዳር 30/2019 ዓ.ም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንና በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶችን በማውገዝ፣ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
በመምሪያው የሴቶች ግንዛቤ ፣ ንቅናቄ ፣ ተሳትፎ ማስፋፊያ ቡድን መሪ አቶ አባተ ተመስገን በበኩላቸው ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ዘለቄታዊ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተና በመሆኑ ይህንን ለመታደግ በዓሉን በንቅናቄ በማክበር ችግሩን ማስቆም ይገባል ብለዋል።
በአለም አቀፍ ደረጃ 30 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ለጾታዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናቶች ያመለክታሉ ያሉት አቶ አባተ ተመስገን ጉዳቱ ከአካላዊና አዕምሯዊ ጉዳት ባለፈ የቤተሰብ ግንኙነትን የማሻከር፣ ማህበራዊ ተሳትፎን የመቀነስ፣ የትምህርት እድልን የማሳጣት እና የኢኮኖሚ ነጻነትን የሚነፍግ በመሆኑ ከወዲሁ ሊወገዝ እንደሚገባ አገንዝበዋል።
ችግሩን ለመቅረፍ መንግስት ፖሊሲዎችን በመንደፍ፣ በየጊዜው ህጎችን እና መመሪያዎችን በማሻሻል ሲተገበር ቆይቷል ያሉት ቡድን መሪው ተጎጅዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችሉ የገቢ ማስገኛ ስራዎችን በትኩረት መስራት ተገቢ ነው ብለዋል።
በንቅናቄ መድረኩ ላይ የመንግስት የስራ ኀላፊዎች ፣ የዘርፉ ባለሙያዎች ፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።
የፎቶ ማዕከል (2)